በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
ቁርኣን 7፥148 የሙሣም ሕዝቦች ከእርሱ መኼድ በኋላ ከጌጦቻቸው ወይፈንን አካልን ለእርሱ "ማግሳት" ያለውን አምላክ አድርገው ያዙ፡፡
وَاتَّخَذَ قَوْمُ مُوسَىٰ مِن بَعْدِهِ مِنْ حُلِيِّهِمْ عِجْلًا جَسَدًا لَّهُ خُوَارٌ
ሙሣ ለአርባ ቀን ወደ ተራራ ከሄደ በኃላ የሙሣ ሕዝቦች ከጌጦቻቸው ወይፈንን አካልን ለእርሱ ማግሳት ያለውን አምላክ አድርገው ያዙ፦
ቁርኣን 7፥148 የሙሣም ሕዝቦች ከእርሱ መኼድ በኋላ ከጌጦቻቸው ወይፈንን አካልን ለእርሱ "ማግሳት" ያለውን አምላክ አድርገው ያዙ፡፡
وَاتَّخَذَ قَوْمُ مُوسَىٰ مِن بَعْدِهِ مِنْ حُلِيِّهِمْ عِجْلًا جَسَدًا لَّهُ خُوَارٌ
"ዒጅል" عِجْل ማለት "ጥጃ" ማለት ሲሆን ይህም ጥጃ "ወይፈን" ነው፥ "ወይፈን" ማለት "ወጣት ጥጃ" ማለት ነው፥ "ጀሠዳ" جَسَدًا ማለት "አካል" ማለት ሲሆን እዚህ ዐውድ ላይ "ምስል" ወይም "ቅርጽ" የሚል ፍቺን ለማመልከት የገባ ነው። የሙሣም ሕዝቦች በምድረበዳ አምላክ አርገው የያዙት ይህ የጥጃ ቅርጽ ማናገር እና መምራት የማይችል ጣዖት ነበረ፦
ቁርኣን 7፥148 እርሱ የማያናግራቸው እና መንገድንም የማይመራቸው መኾኑን አይመለከቱምን? አምላክ አድርገው ያዙት፡፡ በዳዮችም ኾኑ፡፡
أَلَمْ يَرَوْا أَنَّهُ لَا يُكَلِّمُهُمْ وَلَا يَهْدِيهِمْ سَبِيلًا ۘ اتَّخَذُوهُ وَكَانُوا ظَالِمِينَ
ሣሚሪይ የሙሣም ሕዝቦች ካመጡለት ጌጣጌጥ ቅርጽ በመቅረጽ እና የጂብሪል ፈረስ ከረገጠው ዱካ ማለትም ኮቴ ላይ አፈር ዘግኖ በቅርጹ ላይ በማድረግ ማግሳት ያለው ጣዖት ሠርቷል፦
ቁርኣን 20፥96 «ያላዩትን ነገር አየሁ፥ ከመልእክተኛው ዱካም ጭብጥ አፈርን ዘገንኩ፡፡ በቅርጹ ላይ ጣልኳትም፡፡ እንደዚሁም ነፍሴ ሸለመችልኝ» አለ፡፡
قَالَ بَصُرْتُ بِمَا لَمْ يَبْصُرُوا بِهِ فَقَبَضْتُ قَبْضَةً مِّنْ أَثَرِ الرَّسُولِ فَنَبَذْتُهَا وَكَذَٰلِكَ سَوَّلَتْ لِي نَفْسِي
እዚህ አንቀጽ ላይ "መልእክተኛ" የተባለው ጂብሪል ሲሆን ሣሚሪይ የጂብሪል ፈረስ ዱካ የረገጠበትን አፈር ጥጃው ውስጥ ሲበትነው ጥጃው መጓጎር ያለው ሆነ፥ የሙሣ ሕዝቦችም፦ "ይህ አምላካችሁ የሙሣም አምላክ ነው ግን ረሳው" አሉ፦
ቁርኣን 20፥88 ለእነርሱም አካል የኾነ ጥጃን ለእርሱ መጓጎር ያለውን አወጣላቸው፡፡ ተከታዮቹ «ይህ አምላካችሁ የሙሣም አምላክ ነው ግን ረሳው» አሉም፡፡
فَأَخْرَجَ لَهُمْ عِجْلًا جَسَدًا لَّهُ خُوَارٌ فَقَالُوا هَـٰذَا إِلَـٰهُكُمْ وَإِلَـٰهُ مُوسَىٰ فَنَسِيَ
"ኹዋር" خُوَار የሚለው ቃል "ኻረ" خَارَ ማለትም "አገሳ" "ጓገረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ማግሳት" "መጓጎር" ማለት ነው፥ ያ የጥጃ ቅርጽ ልክ እንደ ጥጃ ድምፅ ነበረው። ሚሽነሪዎች፦ "ድምፅ ካለው ሕይወት አለው፥ ሕይወት ካለው ደግሞ ሣሚሪይ ለቅርጹ ሕይወት እንዴት ሰጠው? ሕይወት መስጠት የፈጣሪ ችሎት ብቻ ነው" ብለው ይጠይቃሉ።
፨ሲጀመር አንድ ግዑዝ ነገር ድምፅ ስላለው ሕይወት አለው ብሎ መደምደም ቂልነት ነው፥ ምክንያቱም ዕሩቅ ሳንሄድ ሠው ሠራሽ"artificial" የሆኑት ሮቦት ልክ እንደ ሰው ድምፅ ከማውጣት አልፈው የማሰብ ክህሎት"intelligence" ኖሯቸው ሒሣብ ያሥባሉ፣ ስም እና ቁጥር ይመዘግባሉ፣ መረጃ እና ማስረጃ ያቀብላሉ። ቅሉ ግን ሕይወት የላቸው፥ በተመሳሳይ የሳምራዊው ጥጃ ልክ እንደ ጥጃ ድምፅ ስለነበረው ሕይወት አለው ማለት አይደለም።
፨ሲቀጥል "ሕይወት የነበረው ጥጃ ማስመሰል ነበረ" ቢባል እንኳን ፈጣሪ ሕይወት ከሚሰጥበት ችሎት ጋር የሚመዛዘን፣ የሚነጻር እና የሚለካ አይደለም፥ ምክንያቱም የሙሣ በትር እባብ ሲሆን በተመሳሳይ የፊርዐውን ደጋሚዎች ገመዶቻቸው እና ዘንጎቻቸው የማስለሰል እባቦች አድርገዋል። የሙሣም እባብ የደጋሚዎችን የማስመሰል እባቦች ውጣቸዋለች፦
ቁርኣን 20፥66 «አይደለም ጣሉ» አላቸው፡፡ ወዲያውም ገመዶቻቸው እና ዘንጎቻቸው ከድግምታቸው የተነሳ እነርሱ የሚሮጡ እባቦች ኾነው ወደ እርሱ ተመለሱ፡፡
قَالَ بَلْ أَلْقُوا ۖ فَإِذَا حِبَالُهُمْ وَعِصِيُّهُمْ يُخَيَّلُ إِلَيْهِ مِن سِحْرِهِمْ أَنَّهَا تَسْعَىٰ
ቁርኣን 20፥69 «በቀኝ እጅህ ያለቸውንም በትር ጣል! ያንን የሠሩትን ትውጣለችና፥ ያ የሠሩት ሁሉ የድግምተኛ ተንኮል ነውና፡፡ ድግምተኛም በመጣበት ስፍራ ሁሉ አይቀናውም» አልን፡፡
وَأَلْقِ مَا فِي يَمِينِكَ تَلْقَفْ مَا صَنَعُوا ۖ إِنَّمَا صَنَعُوا كَيْدُ سَاحِرٍ ۖ وَلَا يُفْلِحُ السَّاحِرُ حَيْثُ أَتَىٰ
እኛም በተራችን ጥያቄ እንጠይቃለን። ሕይወት መስጠት የፈጣሪ ብቻ ችሎት ከሆነ ደጋሚዎቹ እንዴት የማስመሰል እባቦች ሠሩ? ይህ ጉዳይ እኮ በባብይልም አለ፦
ዘጸአት 7፥10-12 ሙሴ እና አሮንም ወደ ፈርዖን ገቡ፥ ያህዌህም እንዳዘዛቸው እንዲሁ አደረጉ፤ አሮንም በትሩን በፈርዖን እና በባሮቹ ፊት ጣለ፥ እባብም ሆነች። ፈርዖንም ጠቢባንንና መተተኞችን ጠራ፤ የግብፅም ጠንቋዮች በአስማታቸው እንዲሁ ደግሞ አደረጉ። እያንዳንዳቸውም በትራቸውን ጣሉ፥ እባቦችም ሆኑ፤ የአሮን በትር ግን በትራቸውን ዋጠች።
በሰፈሩት ቁና መሰፈር ይሉካል እንደዚህ ነው፥ ሕይወት መስጠት የፈጣሪ ብቻ ችሎት ከሆነ የግብፅም ጠንቋዮች እንዴት በትራቸውን እባቦች አደረጉ? በመተትስ ቢሆን ሕይወት ያለው እንስሳ ማስመሰል ይቻላልን? ይህንን መልስ ስትሰጡ የሣሚሪይ ጥጃ ድምፅ ያለው ቅርጽ መሆኑ አይደንቃችሁም። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።
✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://t.me/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም