በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

53፥4 እርሱ ንግግሩ የሚወረድ ራእይ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡
إِنْ هُوَ إِلَّا وَحْيٌ يُوحَىٰ

"ሷሒብ" صَاحِب ማለት "ጓደኛ" "ሞክሼ" "ባልደረባ" ማለት ሲሆን ነቢያችን"ﷺ" ለመጡበት ሕዝብ ባልደረባ ነበሩ፥ የመጡበት ሕዝብ ነቢያችንን"ﷺ" እንደተሳሳቱ እና እንደጠመሙ ሰው አሊያም ዕብድ አርጎ ስላያቸው አምላካችን አሏህ፦ "ባልደረባችሁ አልተሳሳተም፤ አልጠመመም። በፍጹም ዕብድ አይደለም" በማለት ለተሳላቂዎች መልስ ይሰጥ ነበር፦

53፥2 ባልደረባችሁ አልተሳሳተም፤ አልጠመመም፡፡
مَا ضَلَّ صَاحِبُكُمْ وَمَا غَوَىٰ
81፥22 ባልደረባችሁ በፍጹም ዕብድ አይደለም፡፡
وَمَا صَاحِبُكُم بِمَجْنُونٍ

የመጡበት ሕዝብ ነቢያችንን"ﷺ" እንደተሳሳቱ እና እንደጠመሙ ሰው አሊያም ዕብድ አርጎ ያየበት ምክንያት ነቢያችን"ﷺ" ያዩት እና የሚናገሩት የሩቅ ነገር ወሬ ነው። ይህ የሩቅ ነገር ወሬ ምን ነበር? "ውኃን ከጥሩ ነገርን ከሥሩ" የሚለውን አገርኛ ብሒል ይዘን እንጀምር! ጂብሪል ወደ ነቢያችን”ﷺ” የሚመጣው በሚወዱት ባልደረባ በዲሕያህ ኢብኑ ኸሊፋህ በሚባል ሰው ተመስሎ ነው፦

ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 66, ሐዲስ 2
አቡ ዑስማን እንደተረከው፦ “ጂብሪል ወደ ነቢዩ”ﷺ” ሲመጣ ኡሙ ሠላማህ ከእርሳቸው ጋር ነበረች፥ ጂብሪል መናገር ጀመረ። ነቢዩም”ﷺ”፦ “ኡሙ ሠላማህ ይህ ማን ነው? አሉ፥ እርሷም፦ “ይህ ዲሕያህ ነው” አለች። ጂብሪል በሄደ ጊዜ እርሷም፦ “ወሏሂ! በነቢዩ”ﷺ” ሑጥባህ ላይ ስለ ጂብሪል ዜና እስኪነግሩን ድረስ ከዲሕያህ በስተቀር ሌላ ማንንም አላሰብኩም ነበር”።
عَنْ أَبِي عُثْمَانَ، قَالَ أُنْبِئْتُ أَنَّ جِبْرِيلَ، أَتَى النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم وَعِنْدَهُ أُمُّ سَلَمَةَ فَجَعَلَ يَتَحَدَّثُ فَقَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم لأُمِّ سَلَمَةَ ‏ “‏ مَنْ هَذَا ‏”‌‏.‏ أَوْ كَمَا قَالَ قَالَتْ هَذَا دِحْيَةُ‏.‏ فَلَمَّا قَامَ قَالَتْ وَاللَّهِ مَا حَسِبْتُهُ إِلاَّ إِيَّاهُ حَتَّى سَمِعْتُ خُطْبَةَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم يُخْبِرُ خَبَرَ جِبْرِيلَ أَوْ كَمَا قَالَ،

ነቢያችን"ﷺ" በመንገድ ጉዞ እያሉ ጂብሪል በተፈጥሮ ቅርጹ ግን ለመጀመሪያ ጊዜ ወርዶ በሰማይ እና በምድር መካከል ተቀምጦ አይተውታል፦

ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 78, ሐዲስ 238
ጃቢ ኢብኑ ዐብደሏህ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰማው ብሎ እንደተረከው፦ “እርሳቸውም እንዲህ አሉ፦ “ከዚያም ወሕይ ወደ እኔ ተቋረጦ ነበር፥ ድንገት እየተጓዝኩኝ እያለ ከሰማይ ድምፅ ሰማሁኝ። እራሴን ቀና አድርጌ ወደ ሰማይ ስመለከት በሒራእ ዋሻ የጎበኘኝ መልአክ በሰማይ እና በምድር መካከል በመንበር ላይ ተቀምጦ አየሁት”።
عَنِ جَابِرُ بْنُ عَبْدِ اللَّهِ، أَنَّهُ سَمِعَ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ “‏ ثُمَّ فَتَرَ عَنِّي الْوَحْىُ، فَبَيْنَا أَنَا أَمْشِي سَمِعْتُ صَوْتًا مِنَ السَّمَاءِ، فَرَفَعْتُ بَصَرِي إِلَى السَّمَاءِ فَإِذَا الْمَلَكُ الَّذِي جَاءَنِي بِحِرَاءٍ قَاعِدٌ عَلَى كُرْسِيٍّ بَيْنَ السَّمَاءِ وَالأَرْضِ ‏”‌‏.‏

ነቢያችን"ﷺ" ጂብሪልን በተፈጥሮ ቅርጹ ለሁለተኛ ጊዜ ያዩት ደግሞ ሲድረቱል ሙንተሃ ላይ ነው፥ “ሲድረቱል ሙንተሃ” سِدْرَة الْمُنْتَهَى የሰባተኛው ሰማይ መጨረሻ ሊታለፍ የማይችል ድንበራዊ ዛፍ ነው፦

53፥14 “በሲድረቱል ሙንተሃ አጠገብ አይቶታል”።
عِندَ سِدْرَةِ الْمُنتَهَىٰ
53፥15 “እርሷ ዘንድ መኖሪያይቱ ጀናህ ያለች ስትኾን”፡፡ عِندَهَا جَنَّةُ الْمَأْوَىٰ
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 53፥13-15 “በሌላይቱም መውረድ ጊዜ በእርግጥ አይቶታል፣ በሲድረቱል ሙንተሃ አጠገብ አይቶታል፣ እርሷ ዘንድ መኖሪያይቱ ጀናህ ያለች ስትኾን” የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ “ጂብሪልን አይቼዋለው፥ ስድስት መቶ ክንፍ አለው”።
وَلَقَدْ رَءَاهُ نَزْلَةً أُخْرَى – عِندَ سِدْرَةِ الْمُنتَهَى – عِندَهَا جَنَّةُ الْمَأْوَى قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله «رَأَيْتُ جِبْرِيلَ وَلَهُ سِتُّمِائَةِ جَنَاحٍ »

“ሙንተሃ” مُنتَهَىٰ የሚለው ቃል “ነሃ” نَهَىٰ ማለትም “ከለከለ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ክልክል” ማለት ነው፥ የሰባተኛው ሰማይ ድንበሩ የሢድራህ ዛፍ ናት። የብርታት ባለቤት የኾነውን ጂብሪል በላይኛውና በግልጹ አድማስ በሲድረቱል ሙንተሃ ላይ ኾኖ ተደላድሎ ሲወርድ አዩት፦

53፥6 “የዕውቀት ባለቤት የኾነው ተደላደለም”፡፡
ذُو مِرَّةٍ فَاسْتَوَىٰ
53፥7 “እርሱ በላይኛው አድማስ ኾኖ”፡፡
وَهُوَ بِالْأُفُقِ الْأَعْلَىٰ
81፥23 “በግልጹ አድማስም በእርግጥ አይቶታል”፡፡
وَلَقَدْ رَآهُ بِالْأُفُقِ الْمُبِينِ

ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ወደ ሲድረቱል ሙንተሃ ሲወጡ አራት ወንዞችን አይተዋል፥ እነዚህም አራት ወንዞች ሠይሓን፣ ጀይሓን፣ ፉራት እና ኒል ናቸው፦

ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 74, ሐዲስ 36አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “አራቱን ወንዞች ባየሁ ጊዜ ወደ ሢድራን ወጣሁኝ”።
عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ رُفِعْتُ إِلَى السِّدْرَةِ فَإِذَا أَرْبَعَةُ أَنْهَارٍ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 53, ሐዲስ 30
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ሠይሓን፣ ጀይሓን፣ፉራት እና ኒል ሁሉም ከጀናህ ወንዞች ናቸው"።
عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ سَيْحَانُ وَجَيْحَانُ وَالْفُرَاتُ وَالنِّيلُ كُلٌّ مِنْ أَنْهَارِ الْجَنَّةِ ‏"‏ ‏.‏

"ሠይሓን" سَيْحَان ማለት "ፊሶን" ማለት ሲሆን፣ "ጀይሓን" جَيْحَان ማለት "ጤግሮስ" ማለት ሲሆን፣ "ፉራት" فُرَات ማለት "ኤፍራስጥ" ማለት ሲሆን፣ "ኒል" نِّيل ማለት ደግሞ "ግዮን" ማለት ነው። አሏህ ሰማይ ላይ ያሉ ሥርዓት በምድር ላይም አርጓል፥ ለምሳሌ፦ በሰባተኛ ሰማይ ከዕባህ ንድፍ የሆነበት ሰባ ሺህ መላእክት አምልኮ የሚፈጽሙበት የደመቀው ቤት "በይቱል መዕሙር" بَيْت الْمَعْمُور ሲባል በተመሳሳይ ምድር ላይ መካህ የሚገኘው የአሏህ ቤት "በይቱል መዕሙር" بَيْت الْمَعْمُور ተብላል፦

52፥4 በደመቀው ቤት እምላለው፡፡
وَالْبَيْتِ الْمَعْمُورِ

በተመሳሳይ አሏህ በሰማይ ላይ እንዳሉት ወንዞች በምድር ላይ ወንዞች አድርጓል፥ ከዚያው ውስጥ በሐዲስ በስም የተጠቀሰ ወንዝ የኤፍራጥስ ወንዝ ነው። ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" መስጴጦምያ ስለሚገኘው ስለ ኤፍራጥስ ወንዝ እንዲህ በማለት ትንቢት ተናግረዋል፦

ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 54, ሐዲስ 38
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ሰዓቲቱ የኤፍራጥስ ወንዝ የወርቅ ተራራ እስኪገልጥ ድረስ ቢደርቅና በእርሱ ጉዳይ ሰዎች ቢዋጉ እንጂ አትቆምም"።
عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ لاَ تَقُومُ السَّاعَةُ حَتَّى يَحْسِرَ الْفُرَاتُ عَنْ جَبَلٍ مِنْ ذَهَبٍ يَقْتَتِلُ النَّاسُ عَلَيْهِ
ሪያዱ አስ-ሷሊሒን መጽሐፍ 18, ሐዲስ 15
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ሰዓቲቱ የኤፍራጥስ ወንዝ የወርቅ ተራራ እስኪገልጥ ድረስ ቢደርቅና ሰዎች በእርሱ ጉዳይ ቢዋጉ እንጂ አትቆምም"።
عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ "‏ لاَ تَقُومُ السَّاعَةُ حَتَّى يَحْسِرَ الْفُرَاتُ عَنْ جَبَلٍ مِنْ ذَهَبٍ فَيَقْتَتِلُ النَّاسُ عَلَيْهِ ‏"‏ ‏.‏

ከሰዓቲቱ ምልክት አንዱ የኤፍራጥስ ወንዝ መድረቅ ከሆነ ይህ ትንቢት በዘመናችን እየተፈጸመ ነው። የኤፍራጥስ ወንዝ እየደረቀ ነው፥ የወርቁ ተራራ ኢንሻሏህ ሲገለጥ ታላቁ ጦርነት ይመጣል። አምላካችን አሏህ ይህንን ገይብ ለነቢዩ"ﷺ" አሳውቋል፥ "ገይብ" غَيْب የሚለው ቃል "ጋበ" غَابَ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "የሩቅ ወሬ" "የሩቅ ሚስጥር" ማለት ነው፦

81፥24 እርሱም በሩቁ ወሬ ላይ ንፉግ አይደለም፡፡
وَمَا هُوَ عَلَى الْغَيْبِ بِضَنِينٍ

"ዘኒን" ظَنِين ማለት "ሰሳች" "ንፉግ" ማለት ሲሆን ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ከአሏህ የተቀበሉትን ገይብ ሳይሰስቱ ነግረውናል። ይህንን ገይብ ከልብ ወለድም አልተናገሩም፥ ንግግራቸው የሚወርድ ግልጠተ መለኮት እንጂ ሌላ አይደለም፦

53፥3 ከልብ ወለድም አይናገርም፡፡
وَمَا يَنطِقُ عَنِ الْهَوَىٰ
53፥4 እርሱ ንግግሩ የሚወረድ ራእይ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡
إِنْ هُوَ إِلَّا وَحْيٌ يُوحَىٰ

አምላካችን አሏህ በነቢያችን"ﷺ" ሡናህ ከሚጠቀሙ ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም