በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
” وَاذْكُرْ فِي الْكِتَابِ إِسْمَاعِيلَ ۚ إِنَّهُ كَانَ صَادِقَ الْوَعْدِ وَكَانَ رَسُولًا نَّبِيًّا ”
በመጽሐፉ ኢሥማዒልን አውሳ፡፡ እርሱ ቀጠሮን አክባሪ ነበረና፡፡ መልክተኛ ነቢይም ነበር፡፡
አምላካችን አሏህ ወደ ኢሥማዒል ወሕይ አውርዷል፥ አሏህ ስለ ኢሥማዒል ሲናገር "በኢሥማዒል... ላይ በተወረደው አመንን በሉ" በማለት ግህደተ-መለኮት ወርዶለት እንደነበር በሡረቱል አለ ዒምራን 3፥84 በሡረቱል በቀራህ 2፥136 እና በሡረቱ አን-ኒስሳእ 4፥163 ላይ ይናገራል። ኢሥማዒል መልክተኛ እና ነቢይ ነበር፥ ቤተሰቦቹንም በሶላት እና በዘካህ ያዝ ነበር፦
” وَاذْكُرْ فِي الْكِتَابِ إِسْمَاعِيلَ ۚ إِنَّهُ كَانَ صَادِقَ الْوَعْدِ وَكَانَ رَسُولًا نَّبِيًّا
በመጽሐፉ ኢሥማዒልንም አውሳ፡፡ እርሱ ቀጠሮን አክባሪ ነበረና፡፡ መልእክተኛ ነቢይም ነበር፡፡
” وَكَانَ يَأْمُرُ أَهْلَهُ بِالصَّلَاةِ وَالزَّكَاةِ وَكَانَ عِندَ رَبِّهِ مَرْضِيًّا
ቤተሰቦቹንም በሶላት እና በዘካህ ያዝ ነበር፡፡ እጌታውም ዘንድ ተወዳጅ ነበር፡፡
"እርሱ ቀጠሮን አክባሪ ነበረ" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! ይህም ቀጠሮ ኢብራሂም ለሥራ በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፤ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?» አለው፤ እርሱም «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አሏህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ» አለ፦
” فَلَمَّا بَلَغَ مَعَهُ ٱلسَّعْىَ قَالَ يَٰبُنَىَّ إِنِّىٓ أَرَىٰ فِى ٱلْمَنَامِ أَنِّىٓ أَذْبَحُكَ فَٱنظُرْ مَاذَا تَرَىٰ ۚ قَالَ يَٰٓأَبَتِ ٱفْعَلْ مَا تُؤْمَرُ ۖ سَتَجِدُنِىٓ إِن شَآءَ ٱللَّهُ مِنَ ٱلصَّٰبِرِينَ
ከእርሱ ጋርም ለሥራ በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፡፡ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?» አለው፡፡ «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ» አለ፡፡
ይህ በእውነት ግልጽ ፈተና ነው፥ አሏህ ኢብራሂምን ልጁን እንዲሠዋ በጠየቀው ቃላት ፈተነው፦
” إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ ٱلْبَلَٰٓؤُا۟ ٱلْمُبِينُ
ይህ እርሱ በእውነት ግልጽ ፈተና ነው፡፡
” وَإِذِ ٱبْتَلَىٰٓ إِبْرَٰهِـۧمَ رَبُّهُۥ بِكَلِمَٰتٍۢ فَأَتَمَّهُنَّ ۖ قَالَ إِنِّى جَاعِلُكَ لِلنَّاسِ إِمَامًۭا ۖ قَالَ وَمِن ذُرِّيَّتِى ۖ قَالَ لَا يَنَالُ عَهْدِى ٱلظَّٰلِمِينَ ”
ኢብራሂምንም ጌታው በቃላት በፈተነው እና በፈጸማቸው ጊዜ አስታውስ! «እኔ ለሰዎች መሪ አድራጊህ ነኝ» አለው፡፡ «ከዘሮቼም አድርግ» አለ፡፡ ቃል ኪዳኔ በዳዮቹን አያገኝም አለው፡፡
ኢብራሂም የተፈተነበት ልጅ ኢሥማዒልን ስለመሆኑ 2፥124 እና 37፥106 ከላይ እና ከታች ዐውደ ንባቡ ያስረዳል፥ "ኢሥማዒል" إِسْمَٰعِيْل የሚለው ስም የሁለት ቃላት ውቅር ነው፥ "ኢሥም" إِسْم የሚለው ቃል "አሥመዐ" أَسْمَعَ ማለት "ሰማ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ይሰማል" ማለት ነው። "ዒል" عِيْل ደግሞ "ኢላህ" إِلَـٰهً ለሚል ምጻረ-ቃል ሲሆን "አምላክ" ማለት ነው፥ በጥቅሉ "ኢሥማዒል" إِسْمَٰعِيْل ማለት "አምላክ ይሰማል" ማለት ነው። ኢብራሂም፦ "ጌታዬ ሆይ! ከመልካሞቹ የሆነን ልጅ ስጠኝ" ብሎ አሏህ ጠይቆ አሏህም ዱዓውን በመስማት ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅ አበሰረው፦
” رَبِّ هَبْ لِى مِنَ ٱلصَّٰلِحِينَ ”
ጌታዬ ሆይ! ከመልካሞቹ የሆነን ልጅ ስጠኝ፡፡
” فَبَشَّرْنَٰهُ بِغُلَٰمٍ حَلِيمٍۢ”
ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰርነው፡፡
” إِنَّ رَبِّي لَسَمِيعُ الدُّعَاءِ
ጌታዬ ልመናን በእርግጥ ሰሚ ነውና፡፡
ኢብራሂም፦ "ጌታዬ ልመናን በእርግጥ ሰሚ ነው" ማለቱ በራሱ ኢብራሂም አሏህን ለምኖ ያገኘው እና ለዕርድ ሲጠየቅ የታገሰ ትእግስተኛ ልጁ ኢሥማዒል መሆኑን ቁልጭ እና ፍንትው አርጎ ያሳያል። አሏህ በልጅ ጉዳይ ኢብራሂም ያበሰረው ሁለት ጊዜ ነው፥ የመጀመሪያው ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም ሲሆን ሁለተኛው በኢሥሐቅ ነው፦
” فَبَشَّرْنَٰهُ بِغُلَٰمٍ حَلِيمٍۢ
ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰርነው፡፡
” وَبَشَّرْنَٰهُ بِإِسْحَٰقَ نَبِيًّۭا مِّنَ ٱلصَّٰلِحِينَ
በኢሥሐቅም አበሰርነው፡፡ ከመልካሞቹ የሆነ ነቢይ ሲሆን፡፡
"በኢሥሐቅ-"ም" የሚለው ይሰመርበት! "ም" የሚለው ጥገኛ ምዕላድ በዐማርኛ ተጨማሪ ነገርን ያሳያል፥ "አበሰርነው" የሚለው ቃል አንድ ዐውድ ላይ ሁለቴ መምጣቱ ኢሥሐቅ እና ከላይ የተጠቀሰው በዱዓ የመጣው ልጅ ይለያያሉ። በተጨማሪም "ወ" وَ የሚለው አርፉል አጥፍ ብስራቱ ሁለት ጊዜ መሆኑን ያሳያል፥ አንደኛው ረድፍ “ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅ” ሲሆን ሁለተኛው ረድፍ “በኢሥሐቅም አበሰርነው” የሚለው ነው። ኢሥሐቅ ደግሞ ኢብራሂም አሏህን ለምኖ የተሰጠ ልጅ ሳይሆን እርሱ እና ሣራህ አንወልድም ብለው ተስፋ በቆረጡበት የተበሰሩት ልጅ ነው፦
” قَالُوا۟ لَا تَوْجَلْ إِنَّا نُبَشِّرُكَ بِغُلَٰمٍ عَلِيمٍۢ ”
«አትፍራ፤ እኛ ዐዋቂ በኾነ ወንድ ልጅ እናበስርሃለን» አሉት፡፡
”قَالَ أَبَشَّرْتُمُونِى عَلَىٰٓ أَن مَّسَّنِىَ ٱلْكِبَرُ فَبِمَ تُبَشِّرُونَ
«እርጅና የደረሰብኝ ከመኾኔ ጋር አበሰራችሁኝን በምን ታበስሩኛላችሁ» አለ፡፡
قَالُوا۟ بَشَّرْنَٰكَ بِٱلْحَقِّ فَلَا تَكُن مِّنَ ٱلْقَٰنِطِينَ«በእውነት አበሰርንህ፡፡ ከተሰፋ ቆራጮችም አትኹን» አሉ፡፡
” فَأَقْبَلَتِ امْرَأَتُهُ فِي صَرَّةٍ فَصَكَّتْ وَجْهَهَا وَقَالَتْ عَجُوزٌ عَقِيمٌ ”
ሚስቱም እየጮኸች መጣች፥ ፊቷንም መታች፡፡ «መካን አሮጊት ነኝ» አለችም።
” وَٱمْرَأَتُهُۥ قَآئِمَةٌۭ فَضَحِكَتْ فَبَشَّرْنَٰهَا بِإِسْحَٰقَ وَمِن وَرَآءِ إِسْحَٰقَ يَعْقُوبَ
ሚስቱም የቆመች ስትኾን አትፍራ አሉት፤ ሳቀችም፡፡ በኢሥሐቅም አበሰርናት፡፡ ከኢስሐቅም በኋላ በልጁ በያዕቁብ አበሰርናት፡፡
ኢብራሂም በኢሥሐቅ ሲበሰር፦ "እርጅና የደረሰብኝ ከመኾኔ ጋር አበሰራችሁኝን በምን ታበስሩኛላችሁ?" ማለቱ ለምኖ ያገኘው ልጅ ሳይሆን ያላሰበው ልጅ መሆኑ አስረግጦና ረግጦ ያሳያል፥ ኢብራሂም እና ሣራህ የተበሰሩት በኢሥሐቅ ብቻ ሳይሆን በልጅ ልጃቸውም በያዕቁብም ነው። ኢብራሂም ኢሥሐቅ ሳይታረድ ተርፎ የልጅ ልጁ ያዕቆብ እንደሚወለድ ካወቀማ እና ይሥሐቅም ያዕቁብ የሚባል ልጅ እንደሚኖረዉ አስቀድሞ ከተበሰረ ልጅህን ዕረድልኝ ብሎ ማዘዙ ፈተናው ትርጉም አልባ ይሆን ነበር፥ ምክንያቱም ልጅህን ዕረድልኝ በእውነት ግልጽ ፈተና ነው። ፈተና ትርጉም የሚኖረው ተፈታኙ የሚፈተነውን የማያውቅ ሲሆን ብቻ እና ብቻ ነው፦
”إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ ٱلْبَلَٰٓؤُا۟ ٱلْمُبِينُ
ይህ እርሱ በእውነት ግልጽ ፈተና ነው፡፡
” وَإِذِ ٱبْتَلَىٰٓ إِبْرَٰهِـۧمَ رَبُّهُۥ بِكَلِمَٰتٍۢ فَأَتَمَّهُنَّ ۖ قَالَ إِنِّى جَاعِلُكَ لِلنَّاسِ إِمَامًۭا ۖ قَالَ وَمِن ذُرِّيَّتِى ۖ
ኢብራሂምንም ጌታው በቃላት በፈተነው እና በፈጸማቸው ጊዜ አስታውስ! «እኔ ለሰዎች መሪ አድራጊህ ነኝ» አለው፡፡ «ከዘሮቼም አድርግ» አለ፡፡ ቃል ኪዳኔ በዳዮቹን አያገኝም አለው፡፡
ሲጀመር ኢብራሂም የበኲር ልጁን ሊሰዋ ሲል በልጁ ፋንታ ዕርድ በግ መቅረቡ እና ይህም ሥርዓት መሠረት በማድረግ ዕርድ የሚካሄደው መካህ እንጂ ሻም አይደለም። ሲቀጥል አሏህ፦ "ቤቴን ለዘዋሪዎቹ፣ ለተቀማጮቹ፣ ለአጎንባሾቹ እና ለሰጋጆቹ አጥሩ" በማለት ቃል ኪዳን የያዘው ከኢብራሂም እና ከኢሥማዒል ጋር ነው፦
” وَإِذْ جَعَلْنَا الْبَيْتَ مَثَابَةً لِّلنَّاسِ وَأَمْنًا وَاتَّخِذُوا مِن مَّقَامِ إِبْرَاهِيمَ مُصَلًّى ۖ وَعَهِدْنَا إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ أَن طَهِّرَا بَيْتِيَ لِلطَّائِفِينَ وَالْعَاكِفِينَ وَالرُّكَّعِ السُّجُودِ
ቤቱንም ለሰዎች መመለሻ እና ጸጥተኛ ባደረግን ጊዜ አስታውስ፡፡ ከኢብራሂምም መቆሚያ መስገጃን አድርጉ፡፡ ወደ ኢብራሂምና ወደ ኢስማዒልም፦ "ቤቴን ለዘዋሪዎቹ፣ ለተቀማጮቹ፣ ለአጎንባሾቹ እና ለሰጋጆቹ አጥሩ" ስንል ቃል ኪዳን ያዝን፡፡
ይህ ጊዜው እዛው ዐውድ ላይ፦ "ኢብራሂምንም ጌታው በቃላት በፈተነው እና በፈጸማቸው ጊዜ" በማለት ይናገራል፥ በዚያን ጊዜ ኢብራሂም እና ኢሥማዒል፦ "ጌታችን ሆይ! ከእኛ ተቀበል፡፡ አንተ ሰሚውና ዐዋቂው አንተ ነህና" በማለት የቤቱን መሠረት ከፍ አርገዋል፦
” وَإِذْ يَرْفَعُ إِبْرَاهِيمُ الْقَوَاعِدَ مِنَ الْبَيْتِ وَإِسْمَاعِيلُ رَبَّنَا تَقَبَّلْ مِنَّا ۖ إِنَّكَ أَنتَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ
ኢብራሂም እና ኢሥማዒል «ጌታችን ሆይ! ከእኛ ተቀበል፡፡ አንተ ሰሚውና ዐዋቂው አንተ ነህና» የሚሉ ሲኾኑ ከቤቱ መሠረቶቹን ከፍ ባደረጉ ጊዜ አስታውስ፡፡
"ኑሡክ" نُسُك ማለት "ሥርዓተ መሥዋዕት" ማለት ሲሆን እዚሁ ቦታ ሥርዓተ መሥዋዕት እንዲፈጸም ወደ አሏህ ዱዓህ ያረጉት ኢብራሂም እና ኢሥማዒል ናቸው፦
” رَبَّنَا وَاجْعَلْنَا مُسْلِمَيْنِ لَكَ وَمِن ذُرِّيَّتِنَا أُمَّةً مُّسْلِمَةً لَّكَ وَأَرِنَا مَنَاسِكَنَا ”
«ጌታችን ሆይ! ለአንተ ታዛዦችም አድርገን፡፡ ከዘሮቻችንም ለአንተ ታዛዦች ሕዝቦችን አድርግ፡፡ ሥርዓተ መሥዋዕቶቻችንንም አሳየን።
"ሀድይ" هَدْي ማለት "የዕርድ እንስሳ" ማለት ሲሆን ይህም እንስሳ ጊደር፣ በግ፣ ፍየል፣ ጥጃ፣ ግመል ነው፥ ይህም ዕርድ የሚካሄደው መካህ ውስጥ ነው፦
” وَأَتِمُّوا الْحَجَّ وَالْعُمْرَةَ لِلَّهِ ۚ فَإِنْ أُحْصِرْتُمْ فَمَا اسْتَيْسَرَ مِنَ الْهَدْيِ”
ሐጅን እና ዑምራንም ለአላህ ሙሉ፤ ብትታገዱም ከሀድይ የተገራውን መሠዋት አለባችሁ፡፡
” جَعَلَ اللَّهُ الْكَعْبَةَ الْبَيْتَ الْحَرَامَ قِيَامًا لِّلنَّاسِ وَالشَّهْرَ الْحَرَامَ وَالْهَدْيَ وَالْقَلَائِدَ ”
አላህ ከዕባን የተከበረውን ቤት ለሰዎች መቋቋሚያ አደረገ፣ የተከበረውን ወር ሀድዩን እና ባለ ምልክቶቹንም መንጋዎች አደረገ፡፡
” فَإِذَا قَضَيْتُم مَّنَاسِكَكُمْ فَاذْكُرُوا اللَّهَ كَذِكْرِكُمْ آبَاءَكُمْ أَوْ أَشَدَّ ذِكْرًا”
የሐጅ ሥራዎቻችሁንም በፈጸማችሁ ጊዜ አባቶቻችሁን እንደምታወሱ ወይም ይበልጥ የበረታን ማውሳት አላህን አውሱ፡፡
"ሥራዎቻችሁ" ለሚለው ቃል የተቀመጠው “መናሢከኩም" مَنَاسِكَكُمْ ሲሆን "ሥርዓተ መሥዋዕቶቻችሁ” ማለት ነው። ኢሥላም ዐቂደቱ አር-ረባንያህ ስንል አርቲ ቡርቲና ቶራ ቦራ የቡና ወሬ ይዘን ሳይሆን የአሏህን ንግግር ደሊል አድርገን ነው። አምላካችን አሏህ ቤቱን ከሚጎበኙት ሑጇጅ ያርገን! አሚን።
ወሠላሙ ዐለይኩም