በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

” قَالُوا اطَّيَّرْنَا بِكَ وَبِمَن مَّعَكَ ۚ قَالَ طَائِرُكُمْ عِندَ اللَّهِ ۖ بَلْ أَنتُمْ قَوْمٌ تُفْتَنُونَ

«በአንተ እና ከአንተ ጋር ባሉት ሰዎች ምክንያት ገደቢሶች ኾን» አሉት፥ «ገደቢስነታችሁ አላህ ዘንድ ነው፤ ይልቁንም እናንተ የምትፈተኑ ሕዝቦች ናችሁ» አላቸው፡፡

ቁርኣን 27:47

ጉሮወሸባ የሚወዱ ሚሺነሪዎች፦ "በኢሥላም አስተምህሮት ሚስት ከፈረስ እና ከቤት ጋር "ገደቢስ ናት" ተብላለች" በማለት ሲቦተረፉ ብዙ ጊዜ ይሰማል፥ ሊሒቃን፦ "ውኃን ከጡሩ፥ ነገርን ከሥሩ" ይላሉና እኛም ከሥሩ ስለ ገደቢስነት በትክክለኛ ምንጨታዊ፣ ስሙር፣ ርቱዕ ሙግት ኢንሻሏህ እንሞግታለን።
"ፈእል" فَأْل ማለት "ገድ" "ዕድል" ማለት ሲሆን "ፈእል" በዋነኝነት የሚያመላክተው አውንታዊ የሆነውን መልካም ገድ"optimism" ነው፦

ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 76, ሐዲስ 69
አቢ ሁራይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው፦ "ጢያራህ የለም፥ መልካሟ ግን ፈእል ነው። እነርሱም፦ "ፈእል ምንድን ነው? ብለው ጠየቁ፥ እርሳቸውም፦ "ከእናንተ አንዱ የሚሰማት መልካም ንግግር ናት" አሉ"። أَنَّ أَبَا هُرَيْرَةَ، قَالَ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏"‏ لاَ طِيَرَةَ، وَخَيْرُهَا الْفَأْلُ ‏"‌‏.‏ قَالُوا وَمَا الْفَأْلُ قَالَ ‏"‏ الْكَلِمَةُ الصَّالِحَةُ يَسْمَعُهَا أَحَدُكُمْ ‏"‌‏.‏

የምንሰማው መልካም ንግግር ሆነ የምንናገረው መልካም ንግግር በራሳችን እና በሚሰማን አውታዊ ተጽእኖ ማሳደር ይችላል፥ መልካም ገድ "ፈእሉ አስ-ሷሊሕ" فَأْلُ الصَّالِح ተብሏል፦

ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 30, ሐዲስ 13
አነሥ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ዐድዋ የለም፥ ጢየራህ የለም። መልካም ፈእል ግን ደስ ይለኛል፥ መልካም ፈእል ደግሞ መልካም ንግግር ነው"። عَنْ أَنَسٍ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ لاَ عَدْوَى وَلاَ طِيَرَةَ وَيُعْجِبُنِي الْفَأْلُ الصَّالِحُ وَالْفَأْلُ الصَّالِحُ الْكَلِمَةُ الْحَسَنَةُ ‏"‏ ‏.‏

"ዐድዋ" عَدْوَى ማለት "በራሱ የሚተላለፍ በሽታ" ማለት ነው፥ በሽታ በአሏህ ፈቃድ እንጂ በራሱ የሚዛመት አይደለምና። "ጢየራህ" طِيَرَة ማለት ደግሞ "በገደቢስ ማመን" ማለት ነው፥ ገደቢስ "ጧኢር" طَائِر ይባላል። አምላካችን አሏህ ወደ ሰሙድ ሕዝብ ነቢዩ ሷሊሕን ሲልከው ሕዝቦቹ፦ "በአንተ እና ከአንተ ጋር ባሉት ሰዎች ምክንያት ገደቢሶች ኾን" አሉት፥ እርሱም፦ "ገደቢስነታችሁ አላህ ዘንድ ነው" አላቸው፦

27፥47 «በአንተ እና ከአንተ ጋር ባሉት ሰዎች ምክንያት ገደቢሶች ኾን» አሉት፥ «ገደቢስነታችሁ አላህ ዘንድ ነው፤ ይልቁንም እናንተ የምትፈተኑ ሕዝቦች ናችሁ» አላቸው፡፡ قَالُوا اطَّيَّرْنَا بِكَ وَبِمَن مَّعَكَ ۚ قَالَ طَائِرُكُمْ عِندَ اللَّهِ ۖ بَلْ أَنتُمْ قَوْمٌ تُفْتَنُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ገደቢሶች ኾን" ለሚለው የገባው የግሥ መደብ "ኢጦየርና" اطَّيَّرْنَا ሲሆን "ገደቢስ" ለሚለው የገባው ደግሞ "ጧኢር" طَائِر ነው። በዐማርኛ "ቢስ" ማለት "አልቦ" "ከንቱ" "ባዶ" ማለት ሲሆን አፍራሽ ቃል ነው፥ ለምሳሌ፦ "ቅጠ ቢስ" "ዋጋ ቢስ" "ዕድለ ቢስ" እንደሚባል "ገደ ቢስ" ማለት "ገድ አልባ" ማለት ነው። ገደቢስነት አሉታዊ ተጽእኖ"pessimism" የሚያመላክት ነው፥ በእርግጥ በገደቢስነት ማመን ሺርክ ነው፦

ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 30, ሐዲስ 7
ዐብደሏህ ኢብኑ መሥዑድ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ጢያራህ ሺርክ ነው፤ ጢያራህ ሺርክ ነው"። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ مَسْعُودٍ، عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ الطِّيَرَةُ شِرْكٌ الطِّيَرَةُ شِرْكٌ ‏"‏

"ሃማህ" هَامَة ማለት "ገድን የምትወስን ወፍ" ተብላ የምትታመን ናት፥ ጥንት ጣዖታውያን ወፏ ካረፈችው ላይ ድንጋይ በመወርወር የምትበርበትን አቅጣጫ በማየት የሚደርስላቸውን እና የሚደርስባቸውን ለማወቅ ይሞክሩ ነበር። በኢሥላም አስተምህሮት ሃማህ ወይም ዐድዋ አሊያም ጢየራህ የለም፥ ጢየራም በፈረስ፣ በሚስት እና በመኖሪያ ቤት ውስጥ አለ ተብሎ የሚታመነው በጃሂሊያህ ዘመን ነው፦

ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 30, ሐዲስ 18
ሠዕድ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ሃማህ የለም፣ ዐድዋ የለም፣ ጢየራህ የለም። ጢየራህ አለ ከተባለ በፈረስ፣ በሚስት እና በመኖሪያ ቤት ውስጥ ነው"። عَنْ سَعْدِ بْنِ مَالِكٍ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم كَانَ يَقُولُ ‏ "‏ لاَ هَامَةَ وَلاَ عَدْوَى وَلاَ طِيَرَةَ وَإِنْ تَكُنِ الطِّيَرَةُ فِي شَىْءٍ فَفِي الْفَرَسِ وَالْمَرْأَةِ وَالدَّارِ ‏"‏ ‏.‏
ኢማም አሕመድ ሙጀለድ 43 ሐዲስ 26034
አቢ ሐሣን እንደተረከው፦ "ሁለት ሰዎች ከበኒ ዓሚር ወደ ዓኢሻህ፦ "አቢ ሁረይራህ ነቢዩ"ﷺ"፦ "ጢየራህ በመኖሪያ ቤት፣ በሚስት እና በፈረስ ነው" ያሉትን የተናገረውን ሰምተናል" አሏት፥ እርሷም በጣም ተናደደች እና እንዲህ አለች፦ "በሙሐመድ ላይ ፉርቃንን ባወረደው ይሁንብኝ! ወደራሳቸው አስጠግተው አልተናገሩም"። ይልቁንም የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ይህንን የሚሉት አህሉል ጃሂሊያህ ናቸው"። عَنْ أَبِي حَسَّانَ ، قَالَ : دَخَلَ رَجُلَانِ مِنْ بَنِي عَامِرٍ عَلَى عَائِشَةَ ، فَأَخْبَرَاهَا أَنَّ أَبَا هُرَيْرَةَ يُحَدِّثُ عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَنَّهُ قَالَ : " الطِّيَرَةُ فِي الدَّارِ وَالْمَرْأَةِ وَالْفَرَسِ "، فَغَضِبَتْ، وَقَالَتْ : وَالَّذِي أَنْزَلَ الْفُرْقَانَ عَلَى مُحَمَّدٍ مَا قَالَهَا رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَطُّ، إِنَّمَا قَالَ : " كَانَ أَهْلُ الْجَاهِلِيَّةِ يَتَطَيَّرُونَ مِنْ ذَلِكَ ".

እዚህ ሐዲስ ላይ "የሚሉት" ለሚለው የግሥ መደብ የገባው ቃል "የተጦየሩነ" يتَطَيَّرونَ ሲሆን የስም መደቡ "ጢየራህ" طِيَرَة ነው። "ዛሊከ" ذَلِكَ የሚለው አመልካች ተውላጠ ስም "ጢየራህ በመኖሪያ ቤት፣ በሚስት እና በፈረስ ነው" የሚለውን ተክቶ የመጣ ነው፥ ስለዚህ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" እንደነገሩን ጢየራህ የጠየሩት አህሉል ጃሂሊያህ እንጂ እራሳቸው ነቢያችን"ﷺ" አይደሉም። እንደውም መልካም ሚስት ገደቢስ ሳትሆን ከዱንያ በረከት በላጭ ናት፦


ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 17, ሐዲስ 76
ዐብደሏህ ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ዱንያ በረከት ነው፥ መልካም ሚስት ግን ከዲንያ በረከት በላጭ ናት"። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ الدُّنْيَا مَتَاعٌ وَخَيْرُ مَتَاعِ الدُّنْيَا الْمَرْأَةُ الصَّالِحَةُ‏"‏ ‏.‏

አሏህ ሂዳያ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም