በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

96፥1 አንብብ በዚያ ሁሉን "በ-"ፈጠረው ጌታህ ስም"፡፡ اقْرَأْ بِاسْمِ رَبِّكَ الَّذِي خَلَقَ

ቁርኣን ሲጀምር የሚነበበው ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም ነው፥ ከአንድ ሡራህ በስተቀር እያንዳንዱ ሡራህ ሲጀምር “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው” በሚል ነው። አንድ ሡራህ ከሌላው ሡራህ የሚለየው “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው” በሚል ቃል ነው፦

ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 398
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ "ነቢዩ”ﷺ” ሁለት ሡራዎች አይለያዩ በመካከላቸው “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው” የሚለው ቃል ወደ እርሳቸው ቢወርድላቸው እንጂ"። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم لاَ يَعْرِفُ فَصْلَ السُّورَةِ حَتَّى تُنَزَّلَ عَلَيْهِ ‏{‏ بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ ‏}

አምላካችን አላህ በጂብሪል ለነቢያችን”ﷺ” “ኢቅራ” اقْرَأْ ማለትም “አንብብ” ብሎ አዟቸዋል፦

18፥27 ከጌታህም መጽሐፍ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ፡፡ وَاتْلُ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِن كِتَابِ رَبِّكَ
29፥45 ከመጽሐፍ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ፡፡ اتْلُ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِنَ الْكِتَابِ
96፥1 አንብብ በዚያ ሁሉን "በ-"ፈጠረው ጌታህ ስም"፡፡ اقْرَأْ بِاسْمِ رَبِّكَ الَّذِي خَلَقَ

"አንብብ በዚያ ሁሉን "በ-"ፈጠረው ጌታህ ስም" የሚለው ይሰመርበት! "በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው" የሚለው ቃል እኛ ሁሉን "በ-"ፈጠረው ጌታህ ስም እንድናነበው የወረደው ነው፥ "በሥመላህ" بَسْمَلَة የሚለው ቃል “በሥመለ” بَسْمَلَ‎ ማለትም “ጠራ” ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን “የአላህን ስም መጥራት” ማለት ነው። ይህም ተዝኪራህ "በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው" የሚል ነው፦

1፥1 በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡ بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيم

ሡረቱል ፋቲሓህ ሰባት አናቅጽ የያዘች እንደሆነች በቁርኣን እና በሐዲስ ተገልጿል፦

15፥87 ከሚደጋገሙ የኾኑን ሰባትን እና ታላቁንም ቁርኣን በእርግጥ ሰጠንህ፡፡ وَلَقَدْ آتَيْنَاكَ سَبْعًا مِّنَ الْمَثَانِي وَالْقُرْآنَ الْعَظِيمَ
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3415
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "አል ሐምዱሊሏህ የቁርኣን "እናት"፣ የመጽሐፉ "እናት" እና ሰባት የተደጋገሙ ናት። عَنِ ابْنِ أَبِي ذِئْبٍ، عَنِ الْمَقْبُرِيِّ، عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْحَمْدُ لِلَّهِ أُمُّ الْقُرْآنِ وَأُمُّ الْكِتَابِ وَالسَّبْعُ الْمَثَانِي ‏

"ሡረቱል ፋቲሓህ ሰባት አንቀጽ ያላት በሥመላህን ጨምሮ ነው ወይስ ሳይጨምር " ለሚለው ጥያቄ መልሱ የሐፍሥ ቂርኣህ በሥመላህን የመጀመሪያው አንቀጽ አርጎ በዚህ መልኩ ያስቀምጧል፦

1፥1 "በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَـٰنِ الرَّحِيمِ
1፥2 ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው። الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ
1፥3 እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ። الرَّحْمَـٰنِ الرَّحِيمِ
1፥4 የፍርዱ ቀን ባለቤት ለኾነው፡፡ مَالِكِ يَوْمِ الدِّينِ
1፥5 አንተን ብቻ እናመልካለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን፡፡ إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ
1፥6 ቀጥተኛውን መንገድ ምራን፡፡ اهْدِنَا الصِّرَاطَ الْمُسْتَقِيمَ
1፥7 የእነዚያን በእነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን፥ በእነርሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውን እና ያልተሳሳቱትን ሰዎች መንገድ ምራን" በሉ፡፡ صِرَاطَ الَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلَا الضَّالِّينَ

የወርሽ ቂርኣህ በሥመላህን መግቢያ አርጎ ተሕሚድን የመጀመሪያው አንቀጽ አርጎ በዚህ መልኩ ያስቀምጧል፦
"በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَـٰنِ الرَّحِيمِ

1፥1 ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው። الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ
1፥2 እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ። الرَّحْمَـٰنِ الرَّحِيمِ
1፥3 የፍርዱ ቀን ንጉሥ ለኾነው፡፡ مَلِكِ يَوْمِ الدِّينِ
1፥4 አንተን ብቻ እናመልካለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን፡፡ إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ
1፥5 ቀጥተኛውን መንገድ ምራን፡፡ اهْدِنَا الصِّرَاطَ الْمُسْتَقِيمَ
1፥6 የእነዚያን በእነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን። صِرَاطَ الَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ
1፥7 በእነርሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውን እና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ ምራን" በሉ፡፡ غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلَا الضَّالِّينَ

በሥመላህ የቁርኣን ክፍል ነው፥ በአንዱ ቂርኣህ በአንቀጽ መልኩ መቀመጡ እና በሌላው ቂርኣህ በአንቀጽ መልኩ አለመቀመጡ ከተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" የመጣ የአነባነብ ስልት"mode of recitation" ነው፦

ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 66, ሐዲስ 13
ኢብኑ ዐባሥ”ረ.ዐ.” እንደተረከው የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "ጂብሪል ለእኔ በአንድ ሐርፍ አቀራር ይቀራልኝ ነበር፥ ከዚያም እኔ በሌላ ሐርፍ እንዲያስቀራኝ ጠየኩት። በተደጋጋሚ ስጠይቀው በሰባት አሕሩፍ በመቅራት ጨመረልኝ። أَنَّ ابْنَ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما ـ حَدَّثَهُ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ أَقْرَأَنِي جِبْرِيلُ عَلَى حَرْفٍ فَرَاجَعْتُهُ، فَلَمْ أَزَلْ أَسْتَزِيدُهُ وَيَزِيدُنِي حَتَّى انْتَهَى إِلَى سَبْعَةِ أَحْرُفٍ ‏”‌‏.‏

የሐፍሥ ሪዋያህ፣ የወርሽ ሪዋያህ፣ የቃሉን ሪዋያህ፣ የዱሪ ሪዋያህ ወዘተ ሲባል ከአሏህ በጂብሪል ለተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" የተወረደ ግልጠተ መለኮት እንጂ ሰዎች የፈጠሩት ልዩነት አይደለም። ይህንን ከተረዳን ዘንዳ በስመላህ የቁርኣን ክፍል ነው፦


ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 4 ሐዲስ 56
አነሥ እንደተረከው፦ "በመካከላችን የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" ሆነው ነበርና ተኙ፥ ከዚያም በፈገግታ እራሳቸውን አነሱ። እኛም፦ "የአሏህ መልእክተኛ ሆይ! ለምን ፈገግ አሉ? አልን፥ እርሳቸውም፦ "ሡራህ ወደ እኔ ተወርዶልኛል" አሉ። እርሳቸው፦ "በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡
እኛ በጣም ብዙ በጎ ነገሮችን ሰጠንህ፣
ስለዚህ ለጌታህ ስገድ፤ በስሙ ሰዋም፣
ጠይህ እርሱ በእርግጥ የተቆረጠው ነው" የሚለውን ቀሩ"። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ بَيْنَا رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ذَاتَ يَوْمٍ بَيْنَ أَظْهُرِنَا إِذْ أَغْفَى إِغْفَاءَةً ثُمَّ رَفَعَ رَأْسَهُ مُتَبَسِّمًا فَقُلْنَا مَا أَضْحَكَكَ يَا رَسُولَ اللَّهِ قَالَ ‏"‏ أُنْزِلَتْ عَلَىَّ آنِفًا سُورَةٌ ‏"‏ ‏.‏ فَقَرَأَ ‏"‏ بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ ‏{‏ إِنَّا أَعْطَيْنَاكَ الْكَوْثَرَ فَصَلِّ لِرَبِّكَ وَانْحَرْ إِنَّ شَانِئَكَ هُوَ الأَبْتَرُ‏}‏ ‏"‏

አያችሁ በሥመላህ የቁርኣን ክፍል ነው። በስመላህ ያለ አንቀጽ መቀመጥ እንደሚችል ደግሞ ይህ ሐዲስ ያሳያል፦

ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 33, ሐዲስ 131
አቢ ሁረይራህ”ረ. ዐ.” እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “እስከሚያስምር ድረስ ለሚቀራው ወዳጁ የሚያማልድ ሠላሳ አናቅጽ የያዘ ሡራህ በቁርኣን ውስጥ አለ፥ እርሱም፦ “ያ ንግሥና በእጁ የኾነው አምላክ የተባረከ(ተመሰገነ) ይሁን” የሚለው ሡራህ ነው”። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ قَالَ ‏”‏ إِنَّ سُورَةً فِي الْقُرْآنِ ثَلاَثُونَ آيَةً شَفَعَتْ لِصَاحِبِهَا حَتَّى غُفِرَ لَهُ ‏{تَبَارَكَ الَّذِي بِيَدِهِ الْمُلْكُ}‏ ‏”‏

ሠላሳ አናቅጽ የያዘ ሡራህ ሡረቱል ሙልክ ሠላሳ የተባለው በስመላህን ሳያካትት ነው። ስለዚህ ሡረቱል ፋቲሓህ ላይ በሥመላህ በአንቀጽ መምጣት እና አለመምጣት ኢሥቲሥናዕ ሆኖ በተለያየ ሪዋያህ መምጣቱ ምንም የትርጉም ልዩነት አያመጣምና እዛ ሰፈር አቧራ ከማስነሳት ይልቅ በመታቀብ "ተሰተሩ" እንላለን። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ

ወሠላሙ ዐለይኩም